Alemayehu Driba
አለማየሁ ድሪባ
Birthplace
Assela
አለማየሁ ድሪባ በ1990 ዓ.ም በአሰላ ከተማ የተወለደ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምር ነው ከትወና ጋር የተዋደደው። አለማየሁ ዲሪባ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቴአትር ጥበብ በ2012 ዓ.ም. የተመረቀ ሲሆን ተዋናይ፣ የፕሮዳክሽን ማናጀር እና አዘጋጅ እንዲሁም በሁለገብነቱ የሚታወቅ የኢትዮጵያ የፊልም ባለሙያ ነው። «ድብብቆሽ» እና «ቁጭት» ባሉ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በፕሮዳክሽን ማኔጀርነት በመሳተፍ ኃላፊነቱን በብቃት ተወጥቷል። በተዋናይነት የተሳተፈባቸው ሥራዎች ደግሞ «የኛ» ተከታታይ ድራማ እና «ቁጭት» ተከታታይ ድራማ ሲሆኑ በፕሮዳክሽን ማኔጀርነት ከተሳተፈባቸው ፊቸር ፊልሞች ውስጥ ጥቂቱ «ያልተበላው እራት»፣ «ከፍቅር በላይ»፣ «ምርኩዜ» እና «ሰርቄሽ» ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በፕሮዲውሰርነት ከሠራቸው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ውስጥ ደግሞ «ስፍራሽ ብዙ» እና «አንድናቸው» ሲሆኑ ፊቸር ፊልሞች ደግሞ «ኃይሌ ገገማው»፣ «ታሪክ» እና «72 ሰዓት» ይገኙበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከ60 በላይ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን የሠራ ባለሙያ ሲሆን። ከዚህም ባሻገር ሲትኮሞችን፣ ፊልሞችን እና የሙዚቃ ክሊፖችን በአዘጋጅነት በመሥራት ለመዝናኛ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
Filmography
Latest first
No filmography yet.
More Filmmakers
Girum Ermias
Actor, Screenplay
Shewaferahu Desalegn
Actor, Assistant Director, Director, Writer
Henok Ayele
Director, Guest Director, Production Advisor, Vocalist
Admasu Kebede
Actor, Director, Second Assistant Director, Writer
Abinet Agonafir
Music, Producer, Sound, Soundtrack, Story, Writer
Amanuel Habtamu
Actor, Producer