Girum Ermias

Actor, Screenplay

Unverified — not yet reviewed against sources

Girum Ermias

ግሩም ኤርሚያስ

Born

March 16, 1978 (age 48)

Birthplace

Addis Ababa

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ገብረሥላሴ በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ካሉ ታዋቂ እና ተወዳጅ መሪ ተዋንያን፣ ደራሲያን እና ዳይሬክተሮች አንዱ ነው። በጥልቀት የመተወን ብቃቱ እና በማኅበረሰቡ ላይ በጎ ተፅዕኖ ያላቸውን ታሪኮች መርጦ በመሥራት ይታወቃል።ግሩም ኤርሚያስ በኢትዮጵያ የፊልም ዓለም ውስጥ በይፋ መሳተፍ የጀመረው በ2005 እ.ኤ.አ አካባቢ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከሃያ በላይ በሚሆኑ ረጅም ልብወለድ ፊልሞች ላይ በዋና ተዋናይነት፣ በደራሲነትና በዳይሬክተርነት በመሳተፍ የራሱን ትልቅ አሻራ አሳርፏል።ፊልሞችን በሚመርጥበት ጊዜ ማኅበረሰባዊ ጠቀሜታ ያላቸው፤ አስተማሪና መረጃ ሰጪ የሆኑ ስክሪፕቶችን ብቻ በጥንቃቄ በመምረጥ ይታወቃል። የሰራቸው ስራዎች • ሔርሜላ (2005)፦ ወደ ዝና እንዲመጣ በር የከፈተለት የመጀመሪያው ተጠቃሽ ፊልሙ ነው። • ስርየት (2007)፦ ከብርቱካን በፍቃዱ ጋር የሠራውና በተመልካች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈለት ሥራው ነው። • ትዝታ፦ የእንስሳት ሐኪም ሆኖ የተወነበትና በተለይ በእንስሳት ሕክምና ባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ አክብሮትና ምስጋና ያስገኘለት ድንቅ ብቃቱን ያሳየበት ፊልም ነው። • ላምባ (2015)፦ በኢትዮጵያ የሕክምና ሥርዓት ላይ ያሉ ተግዳሮቶችንና የካንሰር ሕመምተኞችን ሕይወት የዳሰሰ፣ ከፍተኛ ስሜት የፈጠረ እጅግ ስኬታማ ፊልም ነው። • 400 ፍቅር (2015)፦ ከሩታ መንግሥተአብ ጋር በመሆን ሁለት ገፀ ባሀሪ በመሆን ተውኖበታል። • አማላዩ፣ ሰባ ዘጠኝ (79)፣ በጭስ ተደብቄ እና ሌሎችም በርካታ ተወዳጅ ፊልሞች አሉት፡፡

Filmography

Latest first

More Filmmakers