Amanuel Habtamu

Actor, Producer

Unverified — not yet reviewed against sources

Amanuel Habtamu

አማኑኤል ሀብታሙ

Birthplace

Nazret (Adama)

አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በኢትዮጵያ የፊልም፣ የቴሌቭዥን እና የቲያትር ጥበብ ውስጥ እጅግ ተሰጥኦ ካላቸው እና ተወዳጅ ከሆኑ ባለሙያዎች አንዱ ነው። ከተዋናይነቱ ባሻገር በግጥም አቀራረብ (በተለይ በጦቢያ ግጥም በጃዝ መድረክ) እና በሀገራዊ ስራዎች ላይ ባለው ተሳትፎ በሰፊው ይታወቃል። አማኑኤል ሀብታሙ ተወልዶ ያደገው በናዝሬት ከተማ ነው።ምበመደበኛ ትምህርቱ ያጠናው ዘርፍ ሌላ ቢሆንም ወደ ጥበቡ ዓለም የገባው በአጋጣሚ ነበር። ነገር ግን ባሳየው የላቀ ፍላጎትና ተሰጥኦ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ሰዓቱን በኪነ-ጥበብ ስራዎች ላይ አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። አማኑኤል ለየት ባለ አገላለጽና ጥልቅ ስሜት ግጥሞችን በመድረክ ላይ በማቅረብ ይታወቃል። “ጦቢያ ግጥም በጃዝ” እና በሰይፉ በኢቢኤስ መድረክ ላይ ያቀረባቸው እንደ “የተዘራንበት” እና “ከደሙ ንጹህ ነኝ” ያሉ ማህበራዊና ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ግጥሞቹ በብዙ ሚሊዮን በሚቆጠሩ ተመልካቾች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፈውለታል።በተለያዩ ስኬታማ ፊልሞች እና መድረክ ቲያትሮች ላይ በዋና ገፀ-ባህሪነት እና በፕሮዲውሰርነት ተሳትፏል። ከእነዚህም መካከል፦ • “ረቡኒ” ፊልም፦ በአማኑኤል የትወና ህይወት ውስጥ እጅግ የጎላ አሻራ ያሳረፈ እና በህዝብ ዘንድ በይበልጥ “ልዑል” በሚለው የገፀ-ባህሪ ስሙ እንዲታወቅ ያደረገው ድንቅ ስራው ነው። • “የኮከቡ ሰው” ቲያትር፦ በአገር ውስጥ እና በቅርቡ በውጭ ሀገራት ( በለንደን እና በተለያዩ የእንግሊዝ ከተሞች) ጭምር በመታየት ላይ በሚገኘው የቲያትር መድረክ ላይ ከአንጋፋ ጥበበኞች ጋር በመሆን በከፍተኛ ብቃት እየተወነ ይገኛል። • ማን ያዘዋል? ፣ ታዛ ፣ ጊዜ ቤት ፣ መባ፣ እፉዬ ገላ እና አፊኒ በተሰኙ ፊልሞች ላይ የማይረሱ ገፀ-ባህሪያትን ተጫውቷል።

Filmography

Latest first

Awards & Nominations

More Filmmakers