Director
Unverified — not yet reviewed against sourcesSolomon Bekele Weya
Born
November 1, 1945 (age 81)
Birthplace
Addis Ababa
ሰለሞን በቀለ ወያ በ1945 ዓ.ም በፊንፊኔ (አዲስ አበባ) ልዩ ስሙ ሊደታ በተባለው አካባቢ ተወለደ። ትምህርቱን በተፈሪ መኮንን እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከታትሏል። በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ በመጀመሪያ ወደ ጀርመን በመቀጠልም ወደ እንግሊዝና ፈረንሳይ አቀና። በፈረንሳይ «University de Paris VII» በሥነ-ጽሑፍ እና በቋንቋ ጥናት (Linguistics) በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቀ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ የልጅነት የፊልም ፍላጎቱ እንደገና በማገረሸቱ በፓሪስ ወደሚገኘው ታዋቂው «Ecole National de Cinematography Louis Lumiere» በመግባት የፊልም ስክሪፕት ዝግጅት፣ ካሜራ፣ ኤዲቲንግ እና የፊልም ዳይሬክቲንግ ጥበቦችን ተማረ። በወቅቱ ፕሮፌሰር አሌን ኦቤርት (Professor Allain Aubert) የተባሉ አሰልጣኝ በወጣቱ ኢትዮጵያዊ ተማሪ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር የቻሉ ሲሆን በፊልም ዳይሬክቲንግ ዘርፍ እንዲገፋበትም አበረታተውታል። ሰለሞን ቀደም ሲል በሥነ-ጽሑፍ እና በቋንቋ ጥናት መስክ የቀሰመው እውቀት ለፊልም ሥራ ወሳኝ የሆኑትን የታሪክ አተራረክ እና የንግግር (Dialogue) ጥበብን በሚገባ እንዲያዳብር ረድቶታል። በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ሰለሞን ካዘጋጃቸዉ ዉስጥ «Rotten Existence» (1970) «The Situation of African Cinema» (1972) ይጠቀሳሉ ። በተጨማሪም እስካሁን ድረስ ወደ ፊልም ያልተቀየሩ አራት የስክሪፕት ድርሰቶችን አዘጋጅቷል እነሱም «Leben zu durfen, ein Gluck» (1973) «Hellopia» (1974) «Speak to Me Tomorrow» (1976) «Abeka» (1985) የሚጠቀሱ ናቸዉ ። በአሜሪካ፣ ኢራን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቤልጂየም እና ቼኮዝሎቫኪያ በተደረጉ ከአስራ አምስት በላይ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ፊልሞቹን ይዞ በመቅረብና በዳኝነት (Jury) በመሥራት ተሳትፏል። እንዲሁም የፓን-አፍሪካ የፊልም ባለሙያዎች ፌዴሬሽን (Pan-African Federation of Filmmakers) መሥራች አባል ሲሆን፣ ከ1970 እስከ 1972 በጀርመን የፌዴሬሽኑ ይፋዊ ተወካይ ሆኖ ሰርቷል። በ1983 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር)፣ ሙሉ እውቀትና ብስለት ያገኘው የፊልም ዳይሬክተር እና የስክሪፕት ጸሐፊ ሰለሞን በቀለ፣ ከ22 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በኋላ በሀገር በቀል ጭብጦች ላይ ያተኮሩ ተከታታይ (ዶክመንተሪ) ፊልሞችን መሥራት ጀመረ። ከነሱም ዉስጥ «ብሩህ ተስፋ»(1984) «ሴቶች በኢትዮጵያ» (1985) «ትግል በድርቅ ላይ» (1984-85) እና በሌሎች በርካታ የዶክመንተሪ ፊልሞች ላይ ሙከራዎችን አድርጓል። በዚህም በኢትዮጵያ ፊልም ኮርፖሬሽን ውስጥ የራሱን የሥራ መስክ መፍጠር የቻለ ሲሆን፣ ከዚያ በመነሳትም በኢትዮጵያ የፊልም ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው በ35 ሚሊ ሜትር (35 mm) የቀለም ፊልም የተዘጋጀውን «አስቴር» (ASTER) የተሰኘውን ታዋቂ ፊልም ሰርቶ ለተመልካች አቅርቧል።
Filmography
Latest first
More Filmmakers
Girum Ermias
Actor, Screenplay
Shewaferahu Desalegn
Actor, Assistant Director, Director, Writer
Henok Ayele
Director, Guest Director, Production Advisor, Vocalist
Admasu Kebede
Actor, Director, Second Assistant Director, Writer
Abinet Agonafir
Music, Producer, Sound, Soundtrack, Story, Writer
Amanuel Habtamu
Actor, Producer