Tewodros Teshome

Cinematographer, Director, Writer

Unverified — not yet reviewed against sources

Tewodros Teshome

ቴዎድሮስ ተሾመ

ቴዎድሮስ ተሾመ ከበደ ጥር 29 ቀን 1962 ዓ.ም ቴዎድሮስ በዘጠናዎቹ ላይ የኢትዮጵያን የፊልም ኢንዱስትሪ እንዲያንሰራራ እና የፊልም ሥራዎች እንዲበራከቱ በማድረጉ ይታወቃል። ቴዎድሮስ በራሱ ፊልሞች ላይ ፕሮዲዩሰር፣ደራሲ፣ አዘጋጅ እንዲሁም በተደጋጋሚ ተዋናይ ሆኖ የሚሠራ ሲሆን እንደ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ ስደት ፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ፣ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እና ሃገራዊ ይዘት ያላቸውን ፊልሞች አዘጋጅቷል። ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ የፊልም ታሪክ ከፍተኛ ገቢ ካስገኙ ፊልሞች መካከል ሁለቱን ማለትም «ዓባይ ወይስ ቬጋስ» (Abay vs. Vegas) እና «ቀዝቃዛ ወላፈን» የተሰኙትን ፊልሞች አዘጋጅቷል። በኢትዮጵያ ውስጥ ትልልቅ የፊልም አዘጋጆች ከሆኑት አንዱ ሲሆን«ቴዲ ስቱዲዮ» (Teddy Studios) በተጨማሪም «ሰባስቶፖል ኢንተርቴይንመንት» (ሰባስቶፖል ሲኒማ) ባለቤት ሲሆን፣ ይህም በአገሪቱ የፊልም ዝግጅትና ሥርጭት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዲኖረው አድርጎታል።

Filmography

Latest first

More Filmmakers