Actor
Unverified — not yet reviewed against sourcesDaniel Tegen
ዳንኤል ተገኝ
Birthplace
Addis Ababa
አርቲስት ዳንኤል ተገኝ በኢትዮጵያ የፊልም እና የቴሌቪዥን ድራማ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ታዋቂ ተዋናይ፣ ደራሲ፣ ፕሮዲውሰር እና የበጎ አድራጎት አምባሳደር ነው። በተለይም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው ዝነኛው የ «ገመና» ድራማ ላይ የዶክተር ምስክርን ገፀ-ባህሪ ወክሎ በመጫወት ሰፊ እውቅናን አግኝቷል።ዳንኤል ተገኝ ተወልዶ ያደገው በአዲስ አበባ ነው። ወደ ትወናው ዓለም የገባው በከፍተኛ ፍላጎትና በአጋጣሚዎች ጭምር ሲሆን ለዚህም በኢትዮጵያ ቴአትር ጥበብ ውስጥ ትልቅ ስም ያላቸው የተስፋዬ አበበ (ፋዘር ቤት) ድጋፍ ትልቅ ድልድይ ሆኖለታል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ የፊልሞች፣ የቲቪ ድራማዎች እና የመድረክ ቴአትሮች ላይ በመሳተፍ የራሱን አሻራ ማሳረፍ ችሏል። ከጥበብ ስራው ጎን ለጎንም በተለያዩ ማህበራዊ እና የበጎ አድራጎት ስራዎች (ለምሳሌ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት) ላይ በንቃት ሲሳተፍ ቆይቷል። ከስራዎቹ መካከል ጥቂቶቹ፡- 1. የቴሌቪዥን ድራማዎች (TV Series) • ገመና (፩ እና ፪)፣ ሞጋቾች፣ የማዕበል ዋናተኞች 2. የፊልም ስራዎች (Movies) • ህይወት (የመጀመሪያ የፊልም ስራው) • የሴም ወርቅ (ከትወና በተጨማሪ በደራሲነት እና በፕሮዲዩሰርነት የሰራው ፊልም) • የአውሬ እርግቦች፣ የተፈነቀለ ፍቅር፣ ማክቤል፣ ሄዋን ስታፈቅር፣ ትስስር፣ወደኋላ፣እህት፣ ተስፈኞቹ፣ ሰውዬው፣ እንደ ሀበሻ እና ሌሎችም 3. የመድረክ ቴአትሮች (Stage Plays) • ባቢሎን በሳሎን • የቃቄ ውርዷት • የአሻ ልጅ
Filmography
Latest first
More Filmmakers
Girum Ermias
Actor, Screenplay
Shewaferahu Desalegn
Actor, Assistant Director, Director, Writer
Henok Ayele
Director, Guest Director, Production Advisor, Vocalist
Admasu Kebede
Actor, Director, Second Assistant Director, Writer
Abinet Agonafir
Music, Producer, Sound, Soundtrack, Story, Writer
Amanuel Habtamu
Actor, Producer