Mahmed Dawud

Director, Producer, Screenplay, Writer

Unverified — not yet reviewed against sources

Mahmed Dawud

ማህመድ ዳውድ

Birthplace

Addis Ababa

በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ በደራሲነት፣ በዳይሬክተርነት እና በትወና የሚታወቅ የፊልም ባለሙያ ነው፡፡ ማህሙድ ዳውድ ያደገው በአዲስ አበባ ከተማ ጨርቆስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ለኪነጥበብ ከፍተኛ ፍቅር የነበረው ሲሆን በተለይም በተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ማለትም በድርሰት፣ በትወና እና በሙዚቃ ላይ ይሳተፍ ነበር፡፡ በፊልም ስራው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረበትን እና እንደ አርአያ የሚያየውን ዝነኛውን የፊልም ባለሙያ ኃይሉ ፀጋዬን በመከተልና ከእሱ ጋር አብሮ በመስራት በዘርፉ እውቅናን አትርፏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በፊልም ድርሰትና ዳይሬክቲንግ ላይ በስፋት የሚታወቅ ሲሆን የተወሰኑ ፊልሞች ላይም በትወና ይሳተፋል፡፡ ማህሙድ ዳውድ በርካታ ተወዳጅ የሆኑ የአማርኛና የኦሮምኛ ፊልሞችን ለተመልካች አቅርቧል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡ • ድርሰትና ዝግጅት: «ወደኋላ»፣ «እቴጌ»፣ «ሼፉ 1»፣ «ያነገስከኝ»፣ «ነፃ ትግል»፣ «ምንሼ»፣ እና «ሳማሎ» (በኦሮምኛና አማርኛ የተዘጋጀ)፡፡ • ድርሰት ብቻ የሰራባቸው: «አሜን»፣ «ትራፊኳ» እና «አየሁሽ» የተሰኙት ፊልሞች ይጠቀሳሉ፡፡

Filmography

Latest first

More Filmmakers