Kidist Yilma

Co-Writer, Director, Writer

Unverified — not yet reviewed against sources

Kidist Yilma

ቅድስት ይልማ

Born

February 8, 1978 (age 48)

Birthplace

Addis Ababa

የልጅነት ጊዜዋን በባሌ ጎባ እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በመዘዋወር አሳልፋለች። ትምህርቷን በአዲስ አበባ ከተማ በማጠናቀቅ በራሷ ጥረት የንባብ ክህሎቷን አዳብራለች:: በአባቷ ያነቧችው በነበሩ ጋዜጦች እና መጽሔቶች አማካኝነትም የንባብ ፍላጎቷን አሳድጋለች። በትምህርት ቤት ቆይታዋም በሚኒ ሚዲያ ክበባት በመሳተፍ ለጥበብ ሥራዎች ያላት ፍቅር እያደገ መጥቷል። ሥራዎቿ አብዛኛውን ጊዜ የሀገራችንን ገጠራማ አካባቢዎች የኑሮ ዘይቤ፣ ባህሎች እና ትውፊቶች የሚዳሱ በመሆናቸው ተመልካቹ በቀላሉ ከራሱ ማንነት ጋር ማያያዝ የሚችላቸውና እውነተኛ የህይወት ገጽታዎችን የሚያንጸባርቁ ናቸው። ከሰራቻቸው ስራዎች መካከል • አሀዱ (2001 ዓ.ም.) ከህፃናት አምባ ወጣቶች የሚገጥማቸውን የህይወት ፈተና የሚያሳይ የመጀመሪያ ፊልሟን በአባቷ የገንዘብ ድጋፍ ሰርታ በአንጋፋው ብሔራዊ ቲያትር አስመርቃለች። • ጢባጢቤ (2003 ዓ.ም.) በወጣቶች ዳንስ ላይ ያተኮረውን ይህን ፊልም ዳይሬክት አድርጋለች። • ረቡኒ: በጥበብ አፍቃሪያን ዘንድ በስፋት አሳውቋት እና ስሟን ከፍ አድርጎ ያስጠራላት ተወዳጅ ሥራዋ ነው። • ታዛ (2009 ዓ.ም.) በዳይሬክቲንግ በለዛ አዋርድ፣ ጉማ ፊልም አዋርድ እና በዞዳክ መድረኮች ላይ ተሸላሚ ሆኗል። • እረኛዬ: በአርትስ ቲቪ የተላለፈውና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ይህ የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በስክሪፕት ጽሁፍ እና በማዘጋጀት ተሳትፋበታለች። • ሌሎች ሥራዎች: "ፍቅርና ገንዘብ"፣ "ከዕለታት"፣ "መባ"፣ "ዶቃ" እና "ጀስቲሺያ" የተሰኙ ሥራዎች ለተመልካቾች አድርሳለች።

Filmography

Latest first

Awards & Nominations

More Filmmakers