Actress
Unverified — not yet reviewed against sourcesFikirte Desalegn
ፍቅርተ ደሳለኝ
አንጋፋዋ አርቲስት ፍቅርተ ደሳለኝ (ማሚ) በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ ያገለገለች፤ በብቃቷና በማንነቷ የምትወደድ ድንቅ ተዋናይት፣ ድምፃዊትና ተወዛዋዥ ናት። በተለይም ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ እናት ገፀ-ባህሪን ወክላ በመጫወት ወደር የማይገኝላት አርቲስት ናት። አርቲስት ፍቅርተ ደሳለኝ ከወጣትነቷ ጀምሮ እድሜዋን ሙሉ በኪነ-ጥበብ ውስጥ ያሳለፈች ሲሆን በጡረታ እስክትገለል ድረስ አንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ውስጥ በተዋናይነት፣ በድምፃዊነት እንዲሁም በትወዛዋዥነት አገልግላለች። በ1969 ዓ.ም ናይጀሪያ ዋና ከተማ ሌጎስ በተደረገው ሁለተኛው የአፍሪካና የመላው ዓለም ጥቁር ሕዝቦች የባህልና ኪነ ጥበባት ፌስቲቫል (FESTAC '77) ላይ ሀገሯን ወክለው ከተሳተፉት ጥበበኞች አንዷ ነበረች። ለሀገሯ ጥበብ ላበረከተችው ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽኦ እና ላሳየችው የፈጠራ ብቃት፣ በ10ኛው የጉማ የፊልም ሽልማት (Gumma Award) መድረክ ላይ የክብር የህይወት ዘመን ተሸላሚ (Lifetime Achievement Award) በመሆን ወርቃማ ዋንጫ ተበርክቶላታል። ከፊልም ስራዎቿ የመጀመሪያው “የህሊና ዳኛ” ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ በርካታ የፊልሞችን ሰርታለች። • ታስራለች • ሀገር ስጪኝ • ያ ልጅ • አጼ ማንዴላ • ሰርፕራይዝ • ፊደላዊት • ሹምሽረት • ማንነት • ዱካ • ስሌት • ጓንታናሞ • 400 ፍቅር
Filmography
Latest first
More Filmmakers
Girum Ermias
Actor, Screenplay
Shewaferahu Desalegn
Actor, Assistant Director, Director, Writer
Henok Ayele
Director, Guest Director, Production Advisor, Vocalist
Admasu Kebede
Actor, Director, Second Assistant Director, Writer
Abinet Agonafir
Music, Producer, Sound, Soundtrack, Story, Writer
Amanuel Habtamu
Actor, Producer