Meaza Takele

Costume Designer, Production Manager, Vocalist

Unverified — not yet reviewed against sources

Meaza Takele

መዓዛ ታከለ

ተዋናይት መዓዛ ታከለ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ስመጥር ሴት ተዋንያን ውስጥ አንዷ ነች። መዓዛ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የትያትር ጥበብ ምሩቅ ስትሆን፤ትወናን የጀመረችው በአዲስ አበባ ከተማ በልጅነት ዕድሜዋ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ሀይማኖታዊ ድርማዎችን በመስራት ነበር።በዚህ ጊዜ ታዲያ ችሎታዋን የተመለከቱ የጥበብ ሰዎች« ዲቪ»የሚል ፊልም ላይ እንድተውን መረጧት። በዚህ ሁኔታ ከዓመታት በፊት የተጀመረው የመዓዛ የጥበብ መንገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸራቸውን ጤዛና ድፍረት ፊልሞችን ጨምሮ በበርካታ የመድረክ ትያትሮችና ፊልሞች ላይ ተውናለች።ከነዚህም ውስጥ የጨረቃ ጉዞ፣ከባህር የወጣ ዓሳ፣ዱር ያደረ ፍቅር፣አቤቶ እያሱ ፣የአልማዝ ቀለበት፣ሜዳሊያና ሌሎች የመድረክ ቲያትሮችን እንዲሁም ጤዛ፣ድፍረት ፣ገዳይ ሲያረፋፍድ፣አልዓዛር፣የተወጋ ልብ፣ይሉኝታና በሌሎች በርካታ የፊልም ስራዎች ላይ ተውናለች። ከዚህ ባሻገር አጫጥር የቴሌቪዥን ድራማዎችና የፊልም ማጀቢያ ሙዚቃዎችንም ሰርታለች። «ክብረ አድዋ»በሚል ስያሜ ፌስቲቫል በማዘጋጀት የዓድዋ ድልን የሚዘክር ስራ በሰፊው ትሰራለች። ለባህልና ለታሪክ ትልቅ ቦታ እንዳላት የምትገልፀው መዓዛ «ምህረት» የሚል ትያትር በማዘጋጀትና በመተወን በየዓመቱ የዓድዋ ዋዜማ በኢትዮጵያ በብሄራዊ ቲያትር ለዕይታ ታቀርባለች።የጥበብ ሰው መዓዛ ታከለ የአራት ልጆች እናት ስትሆን፤ ልጅ የማሳደግ ፈተና ከምትወደው የጥበብ ስራዋ ሊነጥላት አልቻለም። ትተውናለች፣የመድረክ ትያትሮችንና የጥበብ ፌስቲቫሎችንም ታዘጋጃለች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከባለቤቷና ከሙያ አጋሯ ከተዋናይ ሚካኤል ሚሊዮን ጋር በመሆን «ሰውኛ» የሚል የኪነጥበብ ድርጅት በመመስረት በባህል በታሪክና በተፈጥሮ ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ይሰራሉ።«ሀገር ማለት ሰው ነው። ሰው ላይ መስራት ደግሞ አትራፊ ነው።» የምትለው መዓዛ በባህልና በታሪክ በማወቅ ረገድ በወጣቱ ዘንድ ያለውን ክፍተት ለመሙላትም ጥንዶቹ ይተጋሉ።

Filmography

Latest first

More Filmmakers