Michael Million

Actor, Director, Producer, Second Assistant Director

Unverified — not yet reviewed against sources

Michael Million

ሚካኤል ሚሊዮን

ለሀገሩና ለባህሉ ከፍተኛ ቦታ ይሰጣል። በዕለት ተዕለት ኑሮውና በአለባበሱ ጭምር ባህሉን ዘካሪና ታሪኩን አክባሪ ነው።ተዋናይ ሚካኤል ሚሊዮን።ሚካኤል የወንዶች ጉዳይ፣ያልታሰበው፣ፔንዱለምና መንሱት የተሰኙ ፊልሞችን ጨምሮ እስካሁን በበርካታ ፊልሞች ላይ ተውኗል።ትውልድና እድገቱ አዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ፤ወደ ትወናው ዓለም ከመግባቱ በፊት በመምህርነት ሙያ ሰርቷል።የጥበብ ፍላጎቱ ከፍ እያለ ሲሄድ ደግሞ የጥበብ ሙያውን በትምህርት ለማገዝ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በመግባት በትያትር ጥበብ ተመርቋል። ይህ የጥበብ ሰው የፊልም ፀሀፊም ነው።በጥበቡ ኢትዮጵያዊ ባህልና አሻራ እንዲኖር ለማድረግም ይጥራል። የአድዋ ድልን የሚዘክር በርካታ ተዋንያን የተሳተፉበት «ምህረት» የተሰኘ ትያትር በማዘጋጀት በብሄራዊ ትያትር ለዕይታ አብቅቷል። ከዓመታት በፊት የጥበብ መንገድን በማስታወቂያ ስራ የተጀመረው ተዋናይ ሚካኤል ሚሊዮን፤እስካሁን አይገባንም፣፣አይራቅ፣ባለጉዳይ፣ፊደላዊት፣፣ያልታሰበው፣የወንዶች ጉዳይ፣የሚሉትን ጨምሮ እስካሁን ከ15 በሚበልጡ ፊልሞችና ስድስት ቲያትሮች ላይ ተውኗል።የጥበብ ስራዎች በበጎም ይሁን በመጥፎ በሰዎች ባህሪ ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ቀላል አይደለም የሚለው ሚካኤል በእሱ ህይወት ላይም ይህንኑ መመለከቱን ይናገራል። ያ በመሆኑ ፊልሞችም ይሁን ቲያትሮች ይዘታቸው ለማኅበረሰቡ ካላቸው ፋይዳ አንፃር መዝኖና በጥንቃቄ መርጦ ነው የሚሰራው። ሚካኤል፤ለሀገሩና ለባህሉ ከፍተኛ ቦታ ይሰጣል። በዕለት ተዕለት ኑሮውና በአለባበሱ ጭምር ባህሉን ዘካሪና ታሪኩን አክባሪ ነው።ይህንን መሰሉን ሀገራዊ አሻራና የተሻለ የጥበብ ፈለግ ይዘው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ልጆቹን በመቅረፅ ላይ መሆኑን ይናገራል።ከአምስት አመት በፊት ደግሞ ከባለቤቱ ጋር በመሆን «ሰውኛ» በሚል ስም በከፈቱት የፕሮዳክሽን ድርጅት «ተፈጥሮ ባህልና ታሪክ ለማንነት በሥ-ጥበብ» በሚል መርህ ሀገራዊ አሻራ ያላቸውንና ትውልድን የሚቀርፁ የጥበብ ስራዎችን የማበረታት ስራ እየሰሩ መሆኑን ይገልጻል።በዚህ ድርጅት የውይይት መድረኮችን፣ ጥናታዊ ፅሁፎችን እንዲሁም ዘጋቢ ፊልሞችን ያዘጋጃል።

Filmography

Latest first

More Filmmakers